ለአክሲዮን ፈላጊዎች በሙሉ!

የኢትዮጲያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባፀደቀው የዳሸን ባንክ አ.ማ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ መሰረት፤ አዲስ አክሲዮን ለመግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፣ በዋናው መስሪያ ቤት በመገኘት በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፈቃድ በተሠጣቸው የአክሲዮን ደላሎች/ኢንቨስትመንት ባንኮች/ በኩል የግብይት ሂሳብ በመክፈት እስከ መጋቢት 07 ቀን 2018 ዓ.ም የአክሲዮን ግዢውን ማከናወን የምትችሉ መሆኑን በደስታ ይገልፃል፡፡
ማሳሰቢያ፡-ሁሉም ባለሃብቶች የዳሸን ባንክ ሙሉ ደንበኛ ሳቢ መግለጫን በሙሉ እንዲያነቡ ይበረታታሉ፤ ለውሳኔ የተቸገሩ ከሆነ በኢትዮጲያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፍቃድከተሰጣቸው ገለልተኛ የፋይናንስ አማካሪዎች ምክር ይጠይቁ፣ የደንበኛ ሳቢ መግለጫው መጽደቅ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ባለሃብቶች እንዲገዙ የተሰጠ ምክር ወይም ድጋፍ ተደርጎ አይወሰድም፡፡ ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) ፈቃድ አግኝቷል፡፡
ለበለጠ መረጃ በአቅራቢያችሁ የሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎችን ይጎብኙ።