“መተግበሪያው ግብይትን ከማቀላጠፉ ባሻገር ቤተሰባዊነት እንዲፈጠር እያደረገ ነው” °የሚት ሲቲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይስሐቅ ተክሌ
“መተግበሪያው ግብይትን ከማቀላጠፉ ባሻገር ቤተሰባዊነት እንዲፈጠር እያደረገ ነው”
°የሚት ሲቲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይስሐቅ ተክሌ
አሁን ላይ በርካታ ምርትና አገልግሎታቸውን የሚሰጡ ተቋማት በዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ ሱቅ ከፍተው የደንበኞችን ህይዎት እያቀለሉ ይገኛሉ፡፡ ከእነኝህ ተቋማት መካከል ደግሞ ንጽህናውን የጠበቀና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ስጋ እያቀረበ የሚገኘው “ሚት ሲቲ” አንዱ ነው፡፡
የሚት ሲቲ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ይስሐቅ ተክሌ በስጋና እንስሳት ተዋጽኦ በማቅረብ ስራ ላይ ከተሰማሩ15 ዓመት እንደሞላቸው ይናገራሉ፡፡ በዘርፉ የረጅም ዓመት ልምድ ያላቸው አቶ ይስሐቅ ዳሸን ሱፐር አፕ እርሳቸውን የመሰሉ የቢዝነስ ሰዎች ስራቸውን ለማሳደግና በሚፈለገው ደረጃ ለማስተዋወቅ ሁነኛ መላ ሆኖ መምጣቱን ያስረዳሉ።
ድርጅታቸው ንጽሕናውን የጠበቀ ስጋ እያቀረበ እንደሚገኝ የሚያስረዱት አቶ ይስሐቅ ዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ የተለያዩ የገበያ ዕድሎችን ፈጥሮልናል ይላሉ። ድርጅታቸው በዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት ላይ ተመዝግቦ መስራቱ የገበያ ተደራሽነታቸውን ለማስፋት አግዞናል የሚሉት የሚት-ሲቲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይስሐቅ አገልግሎታችንን እየተጠቀሙ የሚገኙ ደንበኞች ደስተኛ እንደሆኑ እየነገሩን ነው ብለዋል።
በፋሲካ በዓል ዳሸን ሱፐር አፕ ላይ ሱቅ ከፍተን መስራት ከጀመርን ወዲህ አበረታች የሚባል ውጤት እያየን እንገኛለን የሚሉት አቶ ይስሐቅ፤ ደንበኞች ጊዜና ገንዘባቸውን በአግባቡ ስራ ላይ እንዲያውሉና እንዳይንገላቱ ሆኗል ይላሉ።
ድርጅታቸው በዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ የስጋ ተዋጽኦዎችን ደንበኞች ባሉበት እያቀረበ መሆኑ ‘ዴሊቨሪ’ ለሚሰሩ ሞተረኞችና የታክሲ አገልግሎት ለሚሰጡ አሽከርካሪዎች የስራ ዕድል እንዲፈጥር ማስቻሉንም ተናግረዋል።