Select Page

የዳሸን ኤክስፖ ሶስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን ፣ በዛሬው ዕለት የኮርፖሬት ደንበኞች ትስስር ቀን በሚል የተለያዩ መርሐ-ግብሮች እየተካሄደ ይገኛል።

ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት የተከፈተው የዳሸን ኤክስፖ ሶስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን ፣ በዛሬው ዕለት የኮርፖሬት ደንበኞች ትስስር ቀን በሚል  የተለያዩ መርሐ-ግብሮች እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ-ግብሩ ከዳሸን ባንክ ጋር የሚሰሩ የኮርፖሬት ደንበኞች የታደሙ ሲሆን፣ የኮርፖሬት ክፍል የዘርፍ የስራ ኃላፊዎች የተለያዩ ገለፃዎችን ከማቅረባቸው በተጨማሪ የዐውደ-ርዕይ ጉብኝት ተከናውኗል።

በመጪው ሰኞ የዳሸን ኤክስፖ የሚቀጥል ሲሆን የባንክ ኢንደስትሪው የቴክኖሎጂ ጉዞ ላይ ያተኮሩ ገለጻዎችና ዐውደ-ርእይ ይቀርባል።

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram