ሴቶች አቅማቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙ ባንኩ ድጋፉን እንደሚቀጥል ገለጸ
ዳሸን ባንክ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ለደንበኞቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
የባንኩ የስራ ኃላፊዎች የሴቶች ቀንን በማስመልከት የባንኩ ሴት ደንበኞች የስራ ቦታ ድረስ በመገኘት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በዳሸን ባንክ ቺፍ ኤክሲፒሪየንስ ኦፊር እየሩሳሌም ዋጋው ባንካችን ሴቶች አቅማቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በዛሬው ዕለት ደንበኞች ባሉበት የተከናወነው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት የማድረስ ተግባር ባንኩ ለሴቶች ያለውን አክብሮት የመግለጽና የማበረታታት ግብ እንዳለውም ተናግረዋል።
ዳሸን ባንክ ከሚሠጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያከናወናቸው በሚገኙ ተግባራት በሴቶች የተቋቋሙ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን በተለያዩ መንገዶች እያገዘ እንደሆነም አመላክተዋል።
ዳሸን ባንክ ሁልጊዜም ከጎናችን ስለሆነ እናመሰግናለን ያሉት የሜሪጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢዳር ዘውዴ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በተግባር እያሳየ ይገኛል ብለዋል።
ትኩረት ለሴቶችና ህጻናት ማህበር መስራችና ዳይሬክተር ሲስተር አሣየች ይርጋ ማህበራቸው ተደራራቢ ችግር ያለባቸው ህጻናትና ሴቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ማህበሩ ከዳሸን ባንክ ጋር ከ18 ዓመት በላይ የዘለቀ ደንበኝነት እንዳለው የጠቀሱት ዳይሬክተሯ ባንኩ ለማህበሩ እያደረገ ለሚገኘው ዘርፈ-ብዙ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ፔትኮ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምህረት ተ/ማርያም በበኩላቸው ሴቶችን በሁሉም መስክ ለማብቃት የምንስራቸው ስራዎችን ከባንኩ ጋር እናስቀጥላለን ብለዋል።
