ስለ ሰላም ባዛርና ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ
ዳሸን ባንክ በዛሬው ዕለት በይፋ በተከፈተው ” ስለ ሰላም ባዛርና ኤግዚቢሽን” ላይ አዳዲስ አገልግሎቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል።
ባንኩ “ሾፐርስ እና ትራቭለርስ ክለብ ካርድ” ፣ “አሁን ይብረሩ ቀስ ብለው ይክፈሉ” (Fly now Pay Later) ፣ “ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ” እንዲሁም ሌሎች ከዚህ ቀደም የተዋወቁና አዳዲስና ዘመናዊ አገልግሎቶችን እያስተዋወቀ ይገኛል።
የባዛሩ አዘጋጅ ባሮክ ኤቨንትስ በባዛሩ መክፈቻ ላይ እንዳመላከተው ባዛርና ኤግዚቢሺኑን በቀን 2ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።
200 የሚደርሱ ነጋዴዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው የቀረቡም ሲሆን ዳሸን ባንክ ያቀረባቸው ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎቶች ሸማችና ነጋዴው በቀላሉ እንዲገናኙ ያስችላል።
በተጨማሪም ባንኩ ሙሉ የባንክ አገልግሎቶችን በባዛርና ኤግዚቢሽኑ ላይ እየሰጠ ይገኛል።
ዳሸን ባንክ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተመሳሳይ በተከፈተው የአዲስ ዓመት ባዛርና ኤክስፖ ላይ አዳዲስ አገልግሎቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል።