Select Page

በዳሸን ሱፐር አፕ የቀረበው የዙሪያ ኪው አር አገልግሎት ለንግድ ተቋማትና ደንበኞች መፍትሄ ሆኗል

በርካታ የዲጂታል መደብሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በከተሙበት ዳሸን ሱፐርአፕ የቀረበው የዙሪያ ኪው አር አገልግሎት ለንግድ ተቋማትና ደንበኞች አዲስ መፍትሄ ሆኗል፡፡

በዳሸን ሱፐር አፕ ውስጥ የቀረበው የዙሪያ ኪው አር ኮድ በተለያየ የዙሪያ ተጠቃሚ በሆኑ የንግድ ተቋማት የሚገለገሉ ደንበኞች በቀላሉ ስካን በማድረግ የተለያዩ አገልግሎቶችን መምረጥና ከፍያ መክፈል የሚያስችል ነው፡፡

የኤታ ሶልሽንስ ፒኤልሲ ማርኬቲንግ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ኃይሉ እንዳስታወቁት፣ ለአብነትም እንደ ፒዛ ሃት ባሉ ተቋማት የሚገለገሉ ደንበኞች በዳሸን ሱፐር አፕ ላይ በሚገኘው የዙሪያ ኪው አር ኮድ መተግበሪያ ስካን በማድረግ የፈለጉትን ምግብ የሚያዙ ሲሆን፣ ትዕዛዛቸው ወዲያውኑ ወደ ምግብ አብሳይ (ሼፍ) ደርሶ ከተዘጋጀ በኋላ አስፈላጊውን ክፍያ ፈፅመው አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት ነው፡፡

ይህ አገልግሎት በቀረበ አጭር ጊዜ ከተገልጋዮች እጅግ በጣም አበረታች የሆነ ምላሽ ማግኘቱን የሚገልፁት አቶ ዮሴፍ፣ ዳሸን ባንክና ኤታ ሶልሽንስ ይህንን አገልግሎት በደንብ ለማስተዋወቅ ከተለያዩ የንግድ ተቋማት ጋር ንግግር ከማድረግ ባሻገር የተለያየ የማበረታቻ ዕቅዶች መንደፋቸውን ተናግረዋል፡፡

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram