“በዳሸን ሱፐር አፕ የኢኮሜርስ ግብይት በመጠቀም ምርቶቻችንን ይበልጥ በመሸጥ ላይ ነን” °አቶ ዘላለም መርአዊ የኬሬዥ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር

“በዳሸን ሱፐር አፕ የኢኮሜርስ ግብይት በመጠቀም ምርቶቻችንን ይበልጥ በመሸጥ ላይ ነን”
°አቶ ዘላለም መርአዊ
የኬሬዥ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር
ኬሬዥ ኢትዮጵያ ከዳሽን ባንክ ጋር ላለፉት 22 ዓመታት በደንበኝነት ሲሰራ የቆየ ደርጅት ነው፡፡
ዳሸን ባንክ በቅርቡ ያበለፀገው ሱፐር አፕ የደንበኞችን ፍላጎት ከግምት ውስጥ ያስገባ እና በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ አንድ እርምጃ ቀዳሚነቱን ያስመሰከረበት መሆኑን የኬሬዥ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዘላለም መርአዊ ተናገሩ ፡፡
ኬሬዥ ኢትዮጵያም ከባንኩ ጋር እንደ ቆየ ደንበኛ ሁሉንም የዳሸን ባንክ አገልግሎት በመሞከር በቀዳሚነት እንደሚታወቅም ይገልፃሉ፡፡
ዳሽን ባንክ ሱፐር አፕ የሚሰጠውን አገልግሎት ለደንበኞች ማስተዋወቁ ደንበኞች ኢኮሜርስን በመጠቀም ምርትና አገልግትን ከማስተዋወቅ ጀምሮ ግብይቶችን ይበልጥ መፈፀም የሚያስችል ሆኖ መበልፀጉ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም አመልክተዋል፡፡
“በሱፐር አፕ ኢኮሜርስ ግብይት ምርቶቻቸውን እንዲሸጡ ከተመረጡ ደርጅቶች አንዱ እንደመሆኑ አገልግሎቱን መጠቀም ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ለደንበኞች ምርቶቻችንን ይበልጥ መሸጥ ችለናል፡፡” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በፊት የዲጂታል ባንኪንግ አገልገሎቶች ክፍያዎችን መፈፀም እንጂ የኢኮሜርስ አገልግሎትን አንዲሰጡ ተደርገው የበለፀጉ አልነበሩም፡፡
ዳሸን ባንክ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ቀዳሚ እንደመሆኑ ሱፐር አፕ ካበረከታቸው አገልግሎቶች ውስጥ የኢኮሜርስ ባንክ አግልገሎት ኢንዱስትሪውን የሚያሳድግ አማራጭ ነው፡፡
ኬሬዥ ኢትዮጵያም ጥራት ያላቸው የቆዳ ውጤቶች ማለትም ቦርሳዎች፣ ጃኬቶች፣ ቀበቶዎች እንዲሁም ጫማዎችን በብዛትና በጥራት በማምረት ለደንበኞች በማቅረብ የሚታወቅ ድርጅት ነው፡፡
