Select Page

በዳሸን ባንክ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

ዳሸን ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባስመዘገባቸው ዝርዝር የስራ አፈፃፀሞች ላይ የባንኩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እየተወያዩ ነው።

በዚህ የበጀት አመት የግማሽ አመት አፈፃፀም ላይ ውይይት በተካሄደበት ወቅት በሶስተኛው ሩብ አመት በተለየ መልኩ እንዲተገበሩ በታቀዱ ስራዎች አፈፃፀም ውይይቱ ተጀምሯል።

የባንኩ አጠቃላይ የዘጠኝ  ወራት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ ያተኮረ ውይይትም እየተካሄደ ነው።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ውይይት በቀሪዎቹ የበጀት ዓመቱ ወራት ባንኩ ያስቀመጣቸውን ዕቅዶች በማሳካት አመታዊ ዕቅዱን እውን ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል።

 

 

        

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram