በዳሸን ባንክ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

ዳሸን ባንክ ባለፉት ስድስት ወራት በነበረው አፈፃፀም ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተወያዩ ነው።
በዚህ የበጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም ላይ ውይይት በተካሄደበት ወቅት በሁለተኛው ሩብ አመት በተለየ መልኩ እንዲተገበሩ በታቀዱ ስራዎች አፈፃፀም ውይይቱ ተጀምሯል።
የባንኩ አጠቃላይ የስድስት ወራት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ ያተኮረ ውይይትም እየተካሄደ ነው።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው ውይይት በቀጣይ ስድስት ወራት ባንኩ ያስቀመጣቸውን ዕቅዶች በማሳካት አመታዊ ዕቅዱን እውን ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል
