Select Page

አሃዱ ባንክ ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አሃዱ ባንክ ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የአሃዱ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና ቺፍ ኮርፖሬት ሰርቪስስ ኦፊሰር አቶ ሲሳይ ገብሩ ዳሸን ባንክ  ለፋይናንስ ኢንዱስትሪው እንዲሁም ለተለያዩ ተቋማትና የግል ስራዎች ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን አመልክተዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ለዘርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን ማፍራቱን የገለፁት ተወካዩ እንደ አሃዱ ላሉ በቅርቡ ለተቋቋሙ ባንኩች ትልቅ ልምድ ማካፈል እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

ተወካዩ  ለዳሸን ባንክ ደንበኞች፣ሠራተኞች እና ባለአክሲዮኖች እንኳን ለ30ኛ ዓመት አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ አየለ ተሾመ በበኩላቸው አሃዱ ባንክ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም ከወዲሁ በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ መሆኑን አመልክተው ዳሸን ባንክ ከአሃዱ ባንክ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ባንኩ  የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መልዕክት በማስተላለፉም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ካለፈው ወር ጀምሮ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች  እያከበረ ይገኛል፡፡

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram