Select Page

አማራ ባንክ ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አማራ ባንክ ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ አመት ምክኒያት በማድረግ በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የአማራ ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሃንስ አያሌው በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት ዳሸን ባንክ እንደ አማራ ባንክ ላሉ በቅርቡ የተቋቋሙ ባንኮች አርያና ስኬታማ የሆነ ባንክ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለዳሸን ባንክ ደንበኞች፣ሰራተኞች እና ባለአክሲዮኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የባንኩ ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን በበኩላቸው  የባንኩን ተወካዮች ተቀብለው ባደረጉት  ዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመቱን የሚያከብረው በርካታ ለኢንዱስትሪው አርዓያ ሊሆኑ የሚችሉ ስኬቶችን በማስመዝገብ መሆኑን ጠቁመው እንደ አማራ ባንክ ካሉ በቅርቡ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀሉ ባንኮች ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

አቶ ጥበቡ አማራ ባንክ የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት ምክኒያት በማድረግ መልዕክት በማስተላለፉም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram