Select Page

አግማስ ኢትዮጵያ ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አግማስ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የአግማስ ኢትዮጵያ የፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ኢሳ መሐመድ ዳሸን ባንክ ድርጅቱ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚያደርገው የበጎ አድራጎት ስራ ተከታታይ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርባለሁ ብለዋል፡፡

አቶ ኢሳ  ለዳሸን ባንክ ደንበኞች፣ ሠራተኞች እና ባለአክሲዮኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የባንኩ  ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠባባቂ ቺፍ ኦፊሰር  አቶ አምዱ ሰማን በበኩላቸው ድርጅቱ ውጤታማ የሆነ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማራ መሆኑን ጠቁመው ዳሸን ባንክ መሰል ድርጅቶችን መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል፡፡  አቶ አምዱ  አግማስ ኢትዮጵያ የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ መልዕክት በማስተላለፉም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ካለፈው ወር ጀምሮ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች  እያከበረ ይገኛል፡፡

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram