Select Page

ኤቢኤች ፓርትነርስ እና ዋሽንግተን ሆስፒታል ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የዳሸን ባንክ ደንበኞች የሆኑት ኤቢኤች ፓርትነርስ እና ዋሽንግተን ሆስፒታል ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የሁለቱ ተቋማት ተወካዮች ዳሸን ባንክ ጋር ረጅም ጊዜ በመስራታቸው በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለወደፊትም ከባንኩ ጋር ያላቸውን የስራ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚፈልጉ አመልክተዋል፡፡

ተወካዮቹ ለዳሸን ባንክ ደንበኞች፣ ሠራተኞች እና ባለአክሲዮኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የባንኩ ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ከሁለቱ ተቋማት ጋር ለረጅም ጊዜ የመሰረተው የስራ ግንኙነት አሁን ወደከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ገልፀው ለወደፊትም በተለያዩ የአገልግሎት አማራጮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡ አቶ ጥበቡ ሁለቱ ተቋማት የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መልዕክት በማስተላለፋቸውም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ካለፈው ወር ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች  እያከበረ ይገኛል፡፡

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram