እናት ባንክ ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
እናት ባንክ ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የእናት ባንክ ተወካዮች ዳሸን ባንክ እንደ እናት ባንክ ላሉ ባንኮች ከፍተኛ ልምድ ማጋራት የቻለና የግሉን የባንክ ዘርፍ ለመለወጥ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደሚችል አመልክተዋል፡፡
ተወካዮቹ ለዳሸን ባንክ ደንበኞች፣ሠራተኞች እና ባለአክሲዮኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የባንኩ ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን በበኩላቸው እናት ባንክ በአገራችን የፋይናንስ አካታችነትን ለማሳደግና ለሴቶች የፋይናንስ አቅርቦት ዕድሎችን ይበልጥ ከመፍጠር አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን አመልከተው ባንኩ የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መልዕክት በማስተላለፉም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ካለፈው ወር ጀምሮ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እያከበረ ይገኛል፡፡