ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች-8) በሴቶች ብቻ አገልግሎት በሚሰጠው ዳሸን ኖክ ቅርንጫፍ በድምቀት ተከበረ
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች-8) በሴቶች ብቻ አገልግሎት በሚሰጠው ዳሸን ኖክ ቅርንጫፍ በድምቀት ተከበረ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች-8) በእንስቶች ብቻ አገልግሎት በሚሰጠው ዳሸን ባንክ ኖክ ቅርንጫፍ በድምቀት ተከበረ።
በመርሃግብሩ ላይ የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የባንኩ ደንበኞችና ሌሎች እንግዶች ታድመዋል።
የዳሸን ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ዋና መኮንን (Chief Customer Experience Officer) እየሩሳሌም ዋጋው ባደረጉት ንግግር፣ ሴቶች በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ሚና ቁልፍና ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህንን የሴቶች ወሳኝነት የተረዳው ዳሸን ባንክ ለሴቶች ብቻ የተለየ አገልግሎት ከልዩ የወለድ ጥቅም ጋር አቅርቦ ሴት ደንበኞች እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ አስታውሰው፣ በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትም እንዲሁ ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረገ አገልግሎት ማስተዋወቁን ተናግረዋል።
የዳሸን ባንክ ቺፍ ፒፕል ኦፊሰር ህይወቴ ከፈለኝ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግና ሴቶች በሀገራቸው፣ በድርጅታቸው እንዲሁም በቤተሰባቸው የሚያበረክቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ ለማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ማዕቀፎችን በማካተት በባንኩ የሰው ኃይል ፖሊሲ ሴት ሰራተኞችን ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ ፕሮግራም ቀርፆ ወደ ስራ ከገባ መቆየቱን አስታውቀዋል።
የተቀናጀ ሴቶችን የማብቃት ፕሮግራም “Comprehensive Women Empowerment Program” ቀርፆ ወደ ስራ ያስገባው ዳሸን ባንክ፣ በዚህም ሴቶችን ለስራ የማብቃት፣ የሴቶች ትስስር መፍጠር፣ እንዲሁም የሴቶች የምክክር ፕሮግራሞችን ቀርፆ ወደ ስራ በማስገባት በሁሉም መስክ የሴቶችን ተሳትፎ የማሳደግን እንቅስቃሴ በባንክ ደረጃ እያሳካ እንደሚገኝ ገልፀዋል።