Select Page

“የስነ-ምግባር ጉዳይ ዘወትር ሊዘነጋ አይገባም- አቶ አስፋው ዓለሙ”

የስነ-ምግባር ጉዳይ ዘወትር ሊዘነጋ አይገባም- አቶ አስፋው ዓለሙ”

ሙስናን መከላከል እና ሰነ-ምግባርን ማጽናትን አስመልክቶ ስልጠና ለስራ ኃላፊዎች ታኅሣሥ 24 እና 25/ 2017 ዓ.ም በዳሸን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ተሰጠ።

በስልጠና መርሃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ እንደ ተቋም ስነ-ምግባርን ማስፈንና ሙስናን የመከላከል ባሕላችንን አጠናክረን ማስቀጠል አለብን ብለዋል፡፡

የስነ-ምግባር ጉዳይ ዘወትር መዘንጋት እንደሌለበት ያስታወሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው ባንኩ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ያለውን ጠንካራ ግንኙነት በተሻለ ለማስቀጠል መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ፍትሃዊ ውሳኔዎችን ማሳለፍ እንደሚገባ ያብራሩት አቶ አስፋው ደንበኞችን በስነ-ምግባር ከማስተናገድ ጀምሮ ሌሎች የስራ እንቅስቃሴዎቻችን ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

 

 

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram