Select Page

የአርትስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንት አባላት ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አቀረቡ

የአፍሪካን ሬነሰንስ ቴሌቪዥን (አርትስ ቲቪ) ማኔጀመንት አባላት በዳሸን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ያላቸውን የመልካም ምኞት መልዕክት አቀረቡ፡፡

የአርትስ ቴሌቪዥን የፋይናንስ ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ድሪባ ዳሸን ባንክና አርትስ ቴሌቪዥን ያላቸውን አብሮ የመስራት አጋርነት በማስታወስ እንኳን ለ30ኛ ዓመት የምስረታ በዓላችሁ አደረሳችሁ የሚል መልዕክት አስተላፈዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙን በመወከል ንግግር ያደረጉት የዳሸን ባንክ ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን የአርትስ ቲቪ ማኔጅመንት አባላት እንኳን አደረሳችሁ ለማለት በዳሸን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘታቸው ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ጥበቡ አክለውም ዳሸን ባንክ ከስራ ፈጠራ ጋር ተያይዞ አዳዲስ የቢዝነስ ተሰጥኦዎችን ለማውጣት በቀየሰው የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ከአርትስ ቲቪ ጋር አብሮ በመስራቱ ደስተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

    

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram