የአክሲዮን ሽያጭ ጥሪ ማስታወቂያ
ለዳሸን ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች እና ለአዲስ ባለሃብቶች በሙሉ
ዳሽን ባንክ አ.ማ. በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ኢ.ካ.ገ.ባ) በጸደቀው ደንበኛ ሳቢ መግለጫ እና በተሰጠው ፍቃድ መሰረት፣ ከታኅሣሥ 16 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ስድስት ሽህ ዘጠኝ መቶ ስድስት (2,206,906) መደበኛ አክሲዮኖችን በአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር ሁለት ሽህ ዘጠኝ መቶ (2,900) ሽያጭ የሚያከናዉን መሆኑን በደስታ ይገልጻል፡፡
ለባለአክሲዮኖች ሁሉም ነባር አክሲዮኖች ወደ ኤሌክትሮኒክ ፎርም (ሰነድ አልባነት) ስለሚቀየሩ ብሔራዊ መታወቂያ እና ሁሉንም የአክሲዮን ባለቤትነት ሰርተፍኬት (ማስረጃ) ወይም ከባንኩ የተሰጠ የባለቤትነት ማስረጃ ይዞ መቅረብ ያስፈልጋል፡፡
እንዲሁም ነባር ባለአክሲዮኖችም ይሁን አክሲዮን ለመግዛት የምትፈልጉ አዲስ ባለሃብቶች አክሲዮኖችን ለመግዛት ትችሉ ዘንድ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን እውቅና ከተሰጣቸው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አገበያዮች (ደላሎች) ማለትም ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አክሲዮን ማህበር፤ ከሲቢኢ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አክሲዮን ማህበር፣ አዋሽ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ፣ ኢቲዮ ፊዲሊቲ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አክሲዮን ማህበር፣ገዳ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች አከናዋኝ አ.ማ ወይም ሌላ ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው የሰነደ መዋለ ንዋይ ደላላ የግብይት ሂሳብ (Trading Account) በመክፈት የአክሲዮን ግዥውን እንድትፈፅሙ ባንኩ ጥሪውን ያቀርባል።
ማሳሰቢያ፡ ሁሉም ባለሃብቶች የዳሸን ባንክ ሙሉ ደንበኛ ሳቢ መግለጫን በሙሉ እንዲያነቡ ይበረታታሉ፤ ለውሳኔ የተቸገሩ ከሆነ በኢ.ካ.ገ.ባ ፍቃድ ከተሰጣቸው ገለልተኛ የፋይናንስ አማካሪዎች ምክር ይጠይቁ፣ የደንበኛ ሳቢ መግለጫው መጽደቅ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ባለሃብቶች እንዲገዙ የተሰጠ ምክር ወይም ድጋፍ ተደርጎ አይወሰድም፡፡ ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) ፈቃድ አግኝቷል።
ለበለጠ መረጃ፡ በዳሽን ባንክ አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ግራውንድ ፍሎር ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ሱዳን መንገድ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ፊት ለፊት በአካል በመቅረብ ማናገር ወይም በስልክ ቁጥር: +251 115183091፣ +251 11551 3990 መደወል ይችላሉ፡፡
ዳሸን ባንክ አ.ማ.