የኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር 6ተኛ ዓመታዊ ጉባኤውን በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አካሄደ
የኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር 6ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ አብዱልቃድር ወለላ “ዳሸን ባንክ ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን ላደረገው ትብብር እናመሰግናለን” ብለዋል።
አቶ አብዱልቃድር የማህበሩን የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።
በሪፓርታቸው ማህበሩ በአቅም ግንባታ ዘርፍ አበረታች ውጤቶች መታየታቸውን ያመላከቱ ሲሆን ለማህበሩ አባላት በርካታ ወርክሾፕ እና ስልጠናዎች ከዓለም አቀፍና ሐገር በቀል ተቋማት ጋር በመተባበር መሰጠታቸውን ተናግረዋል።
በ2013 ዓ.ም በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር እና ዳሸን ባንክ የተለያዩ ስራዎችን በትብብር ይሰራሉ። በዚህም ለባለሙያዎች ክህሎታቸውን የሚያሳድጉባቸው ስልጠናዎችን እንዲያገኙ ይደረጋል።
ዳሸን ባንክ ከኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር ቋሚ አባል በመሆን እየሰራ ሲሆን ዘርፉ እንዲያድግ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
