የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራር አባላት ባለፈው በጀት ዓመት ለተገኙ ውጤቶች የባንኩን ደንበኞች፣ የቦርድ አባላት፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላትና አጠቃላይ ማህበረሰብ አመሰገኑ፡፡

የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራር አባላት ባለፈው በጀት ዓመት ለተገኙ ውጤቶች የባንኩን ደንበኞች፣ የቦርድ አባላት፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላትና አጠቃላይ ማህበረሰብ አመሰገኑ፡፡
የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ የ2024/25 በጀት ዓመት መጠናቀቁን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ባንካችን በኢንዱስትሪው መስክ የተከሰቱ የተለያዩ ተግዳሮቶችን ለማለፍ የተደረገው ትብብር የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡
“ዛሬ ላይ ቆመን መጭውን የሥራ ዘመን በሁላችንም የጋራ ጥረት ያቀድነውን የላቀ ውጤት ለማሳካት በጋራና በተናጠል ስላበረከታችሁት አስተዋጽኦ በመጨረሻም ስላገኘነው ፍሬ በመላው የማኔጅመንት አባላትና በራሴ ስም እንኳን ደስ አለን እላለሁ” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአዲሱ በጀት ዓመትም የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ሁሉም የባንኩ ሰራተኞች ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡