የዳሸን ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጅግጅጋ ገቡ

የዳሸን ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጅግጅጋ ገቡ
የዳሸን ባንክ ቺፍ ስትራቴጂክ ኦፊሰር አቶ ኤልያስ ሁሴን፣ የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ መስፍን በዙ እንዲሁም ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጅግጅጋ ገብተዋል።
ለባንኩ ልኡካን የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር በሽር አብዱላሂ፣ የከተማ አስተዳደሩ እና የባንኩ ደንበኞች አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን “እንኳን ደህና መጣችሁ “ብለዋል።
ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ አገልግሎትን በጅግጅጋና አካባቢው እያስተዋወቀ ሲሆን በአገልግሎቱ ዙሪያ በነገው ዕለት ሴሚናር አዘጋጅቷል።
በሴሚናሩም ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ አገልግሎትን አስመልክቶ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ይደረጋል።
ሴሚናሩ በሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች ቀጥሎ ይካሄዳል።