የዳሸን ባንክ ገንዘብ አስተላላፊ ወኪል በመሆን ትርፍዎን ያሳድጉ!

ዳሸን ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (ኢ.ብ.ባ.) ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ አዲሱን “በወኪል ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ዝውውር አገልግሎት” በይፋ ማስጀመሩን ስንገልጽ በኩራት ነው። ይህ ፈጠራ የገንዘብ ልውውጥ አገልግሎት በውጭ የሚኖሩ ገንዘብ ወደ ሀገራቸው የሚልኩበትን መንገድ እና ወኪሎቻችን እነዚህን ወሳኝ ግብይቶች የሚያከናውኑበትን ስርዓት ለመለወጥ ታስቦ የተሰራና በድረ-ገፅ ላይ የተመሰረተ (web-based) መድረክ ነው።
ዓለም አቀፍ የገንዘብ ልውውጦችን ለማመቻቸት ፍቃድ ያላቸው ወኪሎች ከእኛ ጋር በመተባበር ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና ወጪ ቆጣቢ መንገድ እንዲያቀርቡ እንጋብዛለን። ይህ አገልግሎት ከዳሸን ባንክ ጋር ትርፋማ አጋርነትን እያገኙ ሀገርዎን እና ማህበረሰብዎን ለመደገፍ የሚያስችል አቅም ይሰጥዎታል።
በወኪል ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ዝውውር ምንድን ነው?
በወኪል ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ዝውውር ፍቃድ ያላቸው ወኪሎች ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውርን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያመቻቹ የሚያስችል ዘመናዊ ድንበር ዘለል (cross-border) አገልግሎት ነው። ይህ አገልግሎት የአስተላላፊ ቅርንጫፎች ላይ ብቻ ከመመካት ይልቅ፣ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ከውጭ ሀገር እንዲያስተላልፉ ስልጣን ከተሰጣቸው እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመጣው የወኪል አውታራችን በቀላሉ እንዲቀበሉ ምቹ እና ተደራሽ በሆነ መንገድ ያቀርባል።
እንዴት ይሰራል? ቀላልና አስተማማኝ ሂደት
1.ቀላል ምዝገባ: በውጪ የሚገኙ ወኪሎች በልዩ ሁኔታ በተዘጋጀው የወኪል ቋት (portal) በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ። የእኛ ቀለል ያለ ሂደት በፍጥነት እንዲጀምሩ ያደርጋል።
2.ገንዘብ መላክ: በቀላሉ ከውጭ ወደሃገር ገንዘብ ለመላክ ከሚፈልጉ ሰዎች ገንዘብ በመቀበል በሃገር ውስጥ ወዳለ ማንኛውም ባንክ ገንዘብ ለመላክ ያስችላል፡፡
3.በሀገር አቀፍ ደረጃ ክፍያ: በዳሸን ባንክ በኩል ወኪሎች ገንዘቡ ወደ ሀገር ቤት ገንዘብ ሲልኩ በማንኛውም የሀገር ውስጥ ባንክ በኩል ተቀባዮች ገንዘባቸውን እንዲያገኙ ያስችላል።
ከዳሸን ባንክ ጋር አጋር መሆን ለምን ጠቃሚ ነው?
●ተመራጭ የውጭ ምንዛሪ ተመን: ሀገርን እና አጋሮቻችንን ለመደገፍ እንደ ቁርጠኝነት፣ ዳሸን ባንክ በሚያስገቡት የገንዘብ መጠን ሁሉ ላይ ተመራጭ የውጭ ምንዛሪ ተመን ይሰጣል።
ኢትዮጵያን ለመገንባት ከእኛ ጋር እንዲሰሩ እንጋብዝዎታለን። የዳሸን ባንክ የወኪል-ተኮር የገንዘብ ዝውውር አውታርን ይቀላቀሉ፡፡ የዚህ አስደሳች የዲጂታል ለውጥ ወሳኝ አካል ይሁኑ።
ለመመዝገብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡
https://forms.gle/rThMVaSSNedNkGpq9