“የፈጠራና የነቃ ተሳትፎ ወርን ስናከብር ተለዋዋጭ የሆነውን ዓለም ከግምት በማስገባት ሊሆን ይገባል” – አቶ አስፋው ዓለሙ
“የፈጠራና የነቃ ተሳትፎ ወርን ስናከብር ተለዋዋጭ የሆነውን ዓለም ከግምት በማስገባት ሊሆን ይገባል” – አቶ አስፋው ዓለሙ
ዳሸን ባንክ የፈጠራ ባህልና የነቃ ተሳትፎ ወርን አከበረ
ባንኩ በየዓመቱ የሚያከብረው የፈጠራ ባህልና የነቃ ተሳትፎን ለማሳደግ ያለመ መርሐ-ግብር አዘጋጅቷል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ” ባንካችን የፈጠራ ሐሳቦችን ወደ ተግባር ለማስገባት ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር ተግባራዊ ያደረጋቸው ስራዎች አበረታች ናቸው” ብለዋል።
በዚህም የክፍያ ስርዓትን ለማሻሻል የተደረጉ ጥረቶች በመልካም ጎናቸው እንደሚጠቀሱ ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ አበረታች ስራዎችን መተግበር እንደተቻለ አብራርተዋል።
ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።ደንበኛን ማዕከል ያደረገ የፈጠራ ሃሳቦችንን ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የፈጠራና የነቃ ተሳትፎ ወርን ስናከብር ተለዋዋጭ የሆነውን ዓለም ከግምት በማስገባት ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።
በዳሸን ባንክ የባንክ ሞደርናይዜሽን ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ጥላሁን በበኩላቸው የ January ወር የፈጠራና የነቃ ተሳትፎ የምናደርግበት ወር ነው ብለዋል።
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የፋይናንስ ዘርፍ አማካሪ አቶ ሙሉጌታ አለባቸው ፈጠራ በሰው ልጆች ህይዎት ላይ እያሳደሩት ያለውን በጎ አስተዋጽኦ አስመልክቶ ሐሳባቸውን አጋርተዋል።
ዳሸን ባንክ በባንክ ኢንደስትሪው ዘርፍ እየተጫወተ ያለው ሚና ተጠቃሽ እንደሆነ አብራርተዋል።
የባንኩን 29ኛ ዓመት አስመልክቶ የኬክ ቆረሳ ስነ-ስርዓት የተከናወነ ሲሆን የፈጠራ ባሕልን በተመለከተ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።