Select Page

የ ኤ ቲ ኤም አገልግሎት ክፍያ ላይ የተደረገ ለውጥ ስለማሳወቅ

የተከበራችሁ የዳሸን ባንክ ደንበኞች ከባንካችን ጋር ያለዎትን የተቀማጭ ሂሳብ ለማንቀሳቀስ ይረዳዎት ዘንድ ባመለከቱትና ከባንካችን ጋር በገቡት ውል መሠረት የክፍያ ካርድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆንዎ ይታወቃል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት በገቡት ውል መሰረትም ካርድዎን ተጠቅመው ከባንካችን ATM ብር ሲያወጡ በመቶ ብር ወጭ ላይ የሚታሰብ ብር 0.25 የአገልግሎት ክፍያ እንደሚከፍሉ በውሉ ላይ ተቀምጧል፡፡

ባሁኑ ወቅት ባንኩ ገበያውን ያገናዘበ ጥናት በማድረግ ከአሁን በፊት በነበረው የአገልግሎት ክፍያ ላይ መጠነኛ ለውጥ አድረጓል፡፡ በመሆኑም፤ የክፍያ ካርድዎን ተጠቅመው ከባንካችን ATM ገንዘብ ወጭ ሲያደርጉ በመቶ ብር ይከፈል የነበረው ብር 0.25 ወደ ብር 0.35 ከፍ እንዲል የተወሰነ መሆኑን እየገለጽን ይህም ለውጥ እ.ኤ.አ ከየካቲት 1 ቀን 2025 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ አስቀድመን እናሳውቃለን፡፡

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram