ዳሸን ባንክ ለሐጅ ተጓዦች የተቀላጠፈ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል
ባንኩ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ስነ-ስርዓት ለመፈጸም ወደ ሳውዲ ዓረቢያ የሚጓዙ ሁጃጆችን ባሉት ቅርንጫፎች አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡
ዳሸን ባንክ ለሐጅ ተጓዦች ከ80 በላይ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት በሚሰጡ ቅርንጫፎችና ከ800 በላይ በተዘጋጁ መስኮቶች የተቀላጠፈ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
የሐጅ ሐይማኖታዊ ስነ-ስርዓትን ለመፈጸም የሚጓዙ ምዕመናን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የተሰጣቸውን የተመዘገቡበትን መለያ ኮድ ይዘው በመምጣት በባንኩ ሁሉም ቅርንጫፎች ክፍያቸውን በቀላሉ መፈጸም ይችላሉ፡፡
ተጓዥ ምዕመናን በዳሸን ባንክ በኩል ክፍያቸውን ሲፈጽሙ በውጭ ሐገር ቆይታቸው የሚጠቀሙበትን የውጭ ምንዛሬ ያመቻቻል፡፡ ባንኩ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በጋራ እየሰራ ሲሆን ም/ቤቱ በመላው ሐገሪቱ ለሐጅ ምዝገባ ባዘጋጃቸው 30 ማዕከላት ተጓዦችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡
የሐጅ ተጓዦች ከጥር 15 ቀን 2017 ጀምሮ ባሉበት አካባቢ መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን ክፍያቸውን እንግልት ሳይገጥማቸው በዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች በኩል በቀላሉ መፈጸም ይችላሉ፡፡ ምክር ቤቱ የሐጅ ተጓዦችን በፍጥነት በመመዝገብ ጊዜያቸውን እንዲቆጥቡና የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙም ጥሪ አቅርቧል፡፡