ዳሸን ባንክ ለቀጣዮቹ ለ17 ቀናት የሚሳተፍበት የገና ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ በይፋ ተከፈተ

ዳሸን ባንክ ለቀጣዮቹ ለ17 ቀናት የሚሳተፍበት የገና ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ በይፋ ተከፈተ
የባዛሩ አዘጋጅ የሆነው ባሮክ ኤቨንትስ ባዛሩ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትንና ሸማቾችን በቀላሉ ለማገናኘት ምቹ አጋጣሚ እንደሆነ አመላክቷል።
በባዛርና ኤግዚቢሽኑ ባንኮች አገልግሎት እንዲሰጡና ራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ የሚያግዝ እንደሆነም ተመልክቷል።
ዳሸን ባንክ በዚህ ባዛርና አውደ-ርዕይ ላይ የተሟላ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ነጋዴውና ሸማቹ በቀላሉ ግብይት እንዲፈጽሙ እያስቻለ ይገኛል።
የዳሸን ባንክ ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ውብሸት ደርብ ባንኩ የቆዩና አዳዲስ አገልግሎቶችን እያስተዋወቀ ይገኛል ብለዋል።
የባዛሩ ተሳታፊ ከሆኑ አነስተኛ እና ጥቃቅን የንግድ ተቋማት ጋር በቀጣይ በጋራ ለመስራት ውይይቶች እንደሚያደረጉ ጠቁመዋል።
ባዛርና ኤግዚቢሽኑ ከታህሳስ 12- 28/2017 ዓ.ም ይቆያል ።
ዳሸን ባንክ በቅርቡ በኤግዚቢሽን ማዕከል በተከፈተው የገና ባዛር ላይ የተሟላ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ ይታወቃል።


