Select Page

ዳሸን ባንክ ስፖንሰር ያደረገቸው ዝግጅቶች በአሜሪካ ተከናወኑ

ዳሸን ባንክ ስፖንሰር ያደረገቸው የሩጫና የሽልማት መርኅ-ግብሮች በአሜሪካን ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሑድ ተከናውነዋል።

ቅዳሜ እለት የግራንድ አፍሪካ ራን የጎዳና ላይ ሩጫ ተከናውኗል።
ዓመታዊ ሩጫው ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትጵያውያንን ያገናኛል። ተወዳጅነቱም በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል።

ከሩጫው ቀደምት ስፖንሰሮች አንዱ የሆነው ዳሸን ባንክ ከዚህ ቀደም የተከናወኑትን የሩጫ ውድድሮች እንዲሁም የኢምፓክት አዋርድን ሲደግፍ ቆይቷል።

ባንኩ ስፖንሰር ያደረገውና የተለያዩ አበርክቶ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን የሚሸለሙበት የኢምፓክት አዋርድም እሑድ ተካሂዷል።

ዳሸን ባንክ ዝግጅቶቹን ከመደገፉም ባሻገር በአሜሪካን ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን አጠቃላይ የባንኩን እንቅስቃሴ እንዲሁም ዲያስፖራውን ማዕከል ያደረጉ ምርትና አገልግሎቶቹንም ለማስተዋወቅ ችሏል።

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram