ዳሸን ባንክ በሆሳዕና ከተማ ከሚገኙ ደንበኞቹ ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

ዳሸን ባንክ በሆሳዕና ከተማ ከሚገኙ ደንበኞቹ ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ
ዳሸን ባንክ በሆሳዕና ከተማ ከሚገኙ የባንኩ ደንበኞች ጋር በዛሬው ዕለት የምክክር መድረክ አካሄደ።
በመርሃ-ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀዲያ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ዶ/ር በፈቃዱ ገ/ሀና ደሸን ባንክ እንደ መሪ ቃሉ አንድ ረምጃ ቀዳሚ በመሆን በአካባቢው ልማት እንቅሰቃሴ እንዲሁም በማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ተናገረው ይህንን አበረታች እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ታሪኩ ተከተል በበኩላቸው ደሸን ባንክ የደንበኞቹ ሀሳብና ጥየቄ ለመቀበል የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እዚህ ድረስ በአካል በመገኘት ምክክር ማድረጋቸው አድንቀው ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ከዳሸን ባንክ ጋር በትብብር ለመሠራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል ።
በተጨማሪም የዳሽን ባንክ የወላይታ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም መንግስቴ እንደገለጹት፣ በምክክር መድረኩ ላይ የደንበኞች ሀሳብና አስተያየታቸውን እንደ ግብዓት በመጠቀም ባንኩ በቀጣይ ለደንበኞቹ የተሻለና ውጤታማ አገልግሎት ለመሥጠት ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል ።
በምክክር መድረኩ ከደንበኞች ለተነሱ ጥያቄዎች የዳሸን ባንክ MSME ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ ታዳሰ ካሣሁን፣ የዳሸን ባንክ ማርኬቲንግና ብራንዲግ መመሪያ ዳይሬክተር አቶ እንዳለ ገብረሥላሴ ፣ የዳሸን ባንክ ሪቴል ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ አበበ ዘለቀ እና የዳሸን ባንክ የወላይታ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም መንግስቴ አማካኝነት ምላሽና ማብራሪያዎች ተሰጥቷል ።