Select Page

ዳሸን የ“ዘ ባንከር” ሽልማትን ለ13ኛ ጊዜ አሸነፈ

ዳሸን የ“ዘ ባንከር” ሽልማትን ለ13ኛ ጊዜ አሸነፈ

ባንኮችን በተለያዩ የአፈጻጸም መለኪያዎች የሚመዝነው እና የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ የሚያሳትመው ዘ ባንከር መጽሔት ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት በጠቅላላ ለ13ኛ ጊዜ የ2023 የኢትዮጵያ አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል፡፡

ባንካችን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን አነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ተደራሽ በማድረግ የፋይናንስ አካታችነትን መፍጠሩ የ2023ቱን ዘባንከር ሽልማት እንዲያገኝ ካስቻሉት ስኬቶቹ አንዱ ነው። ባንካችን ከቴክኖሎጂ አጋሩ ኤግላይን ጋር ለገበያ ባስተዋወቀው  ‘ዱቤ አለ‘ የተሰኘ በቴክኖሎጅ የታገዘ የዋስትና እና ብድር አቅርቦቱ ለሸማቾች እና አነስተኛ ንግድ አንቀሳቃሾች የሚያቀርበው አገልግሎት ሌላኛው ለሽልማቱ ያበቃው ስኬት ነው፡፡

በቅርቡ ከማስተር ካርድ ጋር ያስተወቅነው ባለ ብዙ መገበያያ ገንዘብ እና ከንክኪ ነፃ ቅድመ ክፍያ ዓለም አቀፍ ካርድ ባንካችንን ለሽልማቱ ካበቁ አያሌ ምክንያቶች ውስጥ ይገኝበታል።

የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋዉ ዓለሙ ሽልማቱን ለንደን ተገኝተዉ ተቀብለዋል፡፡

የእንግሊዙ ዘ ባንከር መጽሄት ከአዉሮፓዉያኑ 1926 ጀምሮ በዓለም አቀፉ የባንክ መስክ ከፍተኛ ተቀባይነት እና ዕውቅና ያለው ህትመት ነው ፡፡

Other Photo Albums

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram