ዳሸን ባንክ በሰባተኛው የታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና እና ሽልማት መርኃ ግብር የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

ዳሸን ባንክ በገቢዎች ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአገር አቀፍ ደረጃ ለ7ተኛ ጊዜ በተካሄደው የታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና መርሐ ግብር ላይ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ፡፡
ሸልማቱን በዳሸን ባንክ የፋይናንስ ዋና መኮንን የሆኑት አቶ አለምነህ አበበ ከጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) እጅ ተቀብለዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ላለፉት አራት ዓመታት በታማኝነት የፕላቲኒየም ሽልማት ላገኙ 30 ልዩ ተሸላሚዎች፤ መንግስት ልዩ ዕውቅናና ሽልማት እንዳዘጋጀላቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ዳሸን ባንክም ከእነዚህ ደርጅቶች ውስጥ ይገኝበታል፡፡
ከ30ዎቹ የፕላቲኒየም ልዩ ተሸላሚዎች መካከል የኢትዮጵያ ኩባንያ ለሆኑት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ከኢትዮጵያ ውጭ በተመረጡ የአፍሪካ ሀገራት ኢንቨስት እንዲያደርጉ መንግሥት የኢንቨስትመንት ዓርማ አድርጎ አብሮ እንደሚሰራ በመርሃግብሩ ላይ ተጠቅሷል።