Select Page

ዳሸን ባንክ በባሌ ሮቤ ከተማ ከደንበኞቹ ጋር መከረ

ዳሸን ባንክ በባሌ ሮቤ ከተማ ከደንበኞቹ ጋር መከረ

ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን (ሸሪክን) አስመልክቶ በባሌ ሮቤ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሴሚናር አካሄደ።

በዳሸን ባንክ የሐዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ አስናቀ ደምሴ ባሌና አካባቢው  የሀገርን ገጽታ በመገንባት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።

አካባቢው በግብርናና ቱሪዝም ያለው  አቅም የሚጠቀስ እንደሆነ አቶ አስናቀ አስረድተዋል። ይህ አቅም ደግሞ ከአካባቢው ተሻግሮ ለሀገር ያለው አበርክቶ ከፍ ያለ እንደሆነም ተናግረዋል።

በባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓህ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኡስታዝ ረመዳን በያን በበኩላቸው  ዳሸን ባንክ የሸሪዓህ መርሆዎችን ያከበሩ አገልግሎቶች በሚፈለገው ደረጃ ለመስጠት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የኤም ኤስ ኤምኢ ዳይሬክተር አቶ ዴታሞ ሬድዋን ባንኩ በእስካሁኑ የ30 ዓመታት ጉዞ የመጣባቸውን የስኬት ጉዞዎችና ከወለድ ነጻ ዘርፍ እየሰጣቸው የሚገኙ አገልግሎቶችንና አሰራሮችን በተመለከተም ገለጻ አድርገዋል።

በዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓ ኮምፕሊየንስና ሪቪው ከፍተኛ ስራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ይመር በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ሸሪዓህን መርህ ያደረጉና ማህበረሰብ-ተኮር አሰራሮችን መዘርጋቱን አመላክተዋል።

የባሌ ሮቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ቢሮ ተወካይ የሆኑት አቶ ሙሐመድ የባ ሸሪክ የማህበረሰቡን የእምነት እሴቶች ያከበሩ አሰራሮችን ዘርግቶ እየሰራ መሆኑ የአካባቢው ኗሪዎችን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ጥያቄን ለመመለስ ከፍተኛ ድርሻ አለው ብለዋል።

ከሴሚኖሩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ሐሳቦች በባንኩ የስራ ኃላፊዎች ምላሸ ሰጥተዋል።

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram