Select Page

ዳሸን ባንክ በቴሌብር የተበደሩ ግለሰቦችን የቅጣት ጊዜ አራዘመ

ዳሸን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በቴሌ ብር አማካኝነት የሠጠውን ብድር በተቀመጠው የመክፈያ ጊዜ መክፈል ሳይችሉ በመቅረታቸው የታሰበባቸውን ቅጣታ አራዝሟል፡፡

ባንኩ ውዝፍ ዕዳ ኖሮባቸው ነገር ግን እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዕዳቸውን ሙሉ በሙሉ ከፍለው ለሚያጠናቅቅ ደንበኞች ቅጣት እንዲነሳላቸው በተወሰነው መሠረት በርካታ ደንበኞች ይህንን ዕድል በመጠቀም ያለባቸውን ዕዳ መዝጋት ችለዋል፡፡

ይህ ለ15 ቀናት ተሰጥቶ የነበረው የቅጣት ስረዛ ጊዜ ታህሳስ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ያበቃ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም የቅጣት ክፍያው መነሳቱ አበረታች ውጠየት ማስመዝገቡን በመግለጹ የቅጣት ስረዛ ጊዜው ከተወሰነ ጊዜ ቢራዘም የሚል ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ዳሸን ባንክ በበኩሉ በቅጣት ስረዛ ጊዜየተገኘው ውጤት አበረታች እንደሆነ የሚምንበት እንደመሆኑ ጊዜው ለተወሰነ ጊዜ አራዝሟል፡፡

ስለሆነም ባንኩ መጪውን የገና በዓል ሰሞን የሚኖረውን ተደራራቢ ወጪ ከግምት በማስገባት የቅጣት የክፍያ ጊዜው ከታህሳስ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ20 ቀናት ማትም እስከ ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲራዘም ወሰኗል፡፡

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram