ዳሸን ባንክ በአጋርነት የተሳተፈበት የ“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ 2018” አርባ ምንጭ ከተማ ታላቁ ሩጫ በድምቀት ተከናወነ
ጤናማ መልክዓ ምድር – ለጤናማ ህይወት’ በሚል መሪ ቃል በአርባ ምንጭ ከተማ የተዘጋጀው የታላቁ ሩጫ ዕውን እንዲሆን ዳሸን ባንክ አጋር ሆኖ የተሳተፈ ሲሆን፣ የመወዳደሪያ ቲሸርቶችንም በልዩ ቅናሽ በዳሸን ሱፐር አፕ ማቅረቡ ይታወሳል።
በዉቧ አርባምንጭ ከተማ በተደረገው የሩጫ ውድድር ፕሮፌሽናል አትሌቶች፣ ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ የተጓዙ ተሳታፊዎችን ጨምሮ ከ3,000 በላይ በተለያየ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የአርባ ምንጭ እና አካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።
የዳሸን የባንክ የወላይታ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም መንግስቴን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በዳሸን ባንክ የተሰየመውን የ16 ዓመት በታች ታዳጊዎች ውድድር የሽልማት መርኃግብርን በመታደም ለአሸናፊዎች የተለያዩ ሽልማቶችን አበርክተዋል።
ከውድድሩ ቀደም ብሎ ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዳሸን ባንክ የወላይታ ዲስትሪክት ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች ከአርባ ምንጭ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘውና አስደናቂ የተፈጥሮ እይታ ባለው በጋንታ ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ መርሐግብር ያከናወኑ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ በአርባምንጭ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ለከተማው ነዋሪዎች የዳሸን ባንክ አዳዲስ አገልግሎቶችን የሚገልፁ የማስተዋወቅ ስራዎች አከናውነዋል።
