ዳሸን ባንክ በይፋ በተከፈተው የ2017 የአዲስ ዓመት ባዛርና ኤክስፓ ላይ አዳዲስ አገልግሎቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል
የ2017 አዲስ አመት ባዛርና ኤክስፓ በይፋ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል። በባዛሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የዳሸን ባንክ ደንበኞች በበኩላቸው ዳሸን ባንክ አሁን ላይ እያስተዋወቃቸው የሚገኙ አዳዲስ አገልግሎቶች ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ የፋይናንስ ዘርፋን ቀልጣፋ እንደሚያደርገው አስረድተዋል።
ዳሸን ባንክ እየተሳተፈበት በሚገኘው የ2017 ባዛርና ኤክስፓ ላይ በቅርቡ ወደ ስራ ያስገባቸውን ትራቭለርስ ኤንድ ሾፐርስ ካርዶች፣ ከወለድ -ነፃ ዱቤ አለ ፣ አሁን ይብረሩ ቆይተው ይክፈሉ እና ሌሎች አገልግሎቶችን እያስተዋወቀ ይገኛል።
የባንኩ አዳዲስና ነባር ደንበኞች እነኝህንና ሌሎች አገልግሎቶችን ይጠቀሙ ዘንድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ከባዛርና ኤክስፓ ተሳታፊዎች የሚኘውን የውጭ ምንዛሬ የማሰባሰብ፣ ለተሳታፊዎች ስለ ዳሸን ባንክ ቀልጣፋና ዘመኑን የዋጁ አገልግሎቶችን በስፋት የማስተዋወቅ ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነ ተመላክቷል።
ባዛርና ኤክስፓውን ታሜሶል ኮምኒኬሽንስ ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመሆን ያዘጋጀው ሲሆን ለ 20 ቀናት በሚቆየው በዚህ ደማቅ ሁነት 5መቶ ሺህ የሚደርሱ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል።