Select Page

ዳሸን ባንክ በ”ዱቤ አለ” ከ2 ቢሊየን ብር በላይ አበደረ

ዳሸን ባንክ በ”ዱቤ አለ” አገልግሎቱ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ለደንበኞች አበደረ።

“አሁን ይሸምቱ፣ ቆይተው ይክፈሉ!” የሚል መሪ ቃል ያለው  ይህ አልገልግሎት ከ466,000 በላይ የሆኑ ደንበኞች በ856 ቅርንጫፎች  ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን፣ 20,000 የሚሆኑ ነጋዴዎች ደግሞ ምርትና አገልግሎታቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

“ዱቤ አለ” ዳሸን ባንክ ከኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ምርትና አገልግሎት የሚያቀርቡ የንግድ ድርጅቶች ጋር በጥምረት ያቀረበዉ በቴክኖሎጂ የታገዝ የዱቤ አሰራር ነው።

ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ የጀመረው ይህ አገልግሎት፣ ህብረተሰቡ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችንና በርካታ አገልግሎቶችን በ3 ወር፣ በ6 ወርና በ12 ወር በሚመለስ ዱቤ በወለድና ያለወለድ መግዛት የሚያስችል አማራጭ ነው፡፡

ደንበኞች መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር ወይም ከአፕ ስቶር በማውረድ ለአገልግሎቱ መመዝብ ይችላሉ፡፡ ከተመዘገቡ በኋላም ወደ ዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ በማምራት የዱቤ ገደብ ማስፈቀድና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

ባንኩ ተለምዷዊውን ዱቤ በቴክኖሎጂ ከማዘመን በተጨማሪ በሸማቾች እና የንግድ ተቋማት መካከል መተማመን በመፍጠር ሸማቾች ፍላጎታቸውን በጊዜው እንዲሞሉ አምራቾችና እና አገልግሎት አቅራቢዎችም ሽያጫቸውን እንዲያሳድጉ የሚያግዝ ነው።

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram