Select Page

ዳሸን ባንክ በጅግጅጋ 500 ዳግም ጥቅም ላይ የሚውል የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ

ዳሸን ባንክ በጅግጅጋ 500 ዳግም ጥቅም ላይ የሚውል የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ

ባንኩ ለጅግጅጋ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (ፓድ) ድጋፍ አድርጓል።

በዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ መስፍን በዙ  ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ያስቀጥላል ብለዋል ።

የሱማሌ ክልል የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዘሃራ አብዲ ዳሸን ባንክ ዛሬ ያበረከተው ድጋፍ ሴት ተማሪዎችን የሚያበረታታ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ኃላፊዋ ባንኩ  ለሴቶች ትኩረት በመስጠት እያበረከተ ላለው ጉልህ አስተዋጽኦ በቀላል የሚታይ አይደለም፣ ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል። ቢሯቸው ከባንኩ ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ እንደሆነም አመላክተዋል።

የፓድ አምራች የሆነው ሐንስ ኬር ስራ አስኪያጅ ሐናን አሕመድ ከዳሸን ባንክ ጋር በመስራቴ ክብር ይሰማኛል ያሉ ሲሆን  ከዚህ ቀደም  በደሴ፣አ/አ፣መቀሌና ሌሎች የክልል ከተሞች ከ7 ሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በበኩላቸው “ዳሸን ባንክ ላደረገልን ድጋፍ እናመሰግናለን” ብለዋል።

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram