Select Page

ዳሸን ባንክ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

ዳሸን ባንክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ድጋፍ እንዲውል የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበርክቷል።
 
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን ዳሸን ባንክ በዞኑ ነዋሪዎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በድጋሚ ገልፀው ባንኩ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለመርዳት በሚደረገው አገራዊ ጥረት የበኩሉን ድጋፍ ለማቅረብ ስፍራው ድረስ መገኘቱን አመልክተዋል።
 
ዳሸን ባንክ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረትም የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ አቶ ጥበቡ ገልጸዋል።
 
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ አጌና ድጋፉን ይዘው በስፍራው ለተገኙ የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራሮች አደጋው ስላደረሰው ጉዳት ገለፃ ከሰጡ በኋላ ዳሸን ባንክ በአካባቢው ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጀምሮ ላበረከተው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
 
ከዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን በተጨማሪ የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ ኤልያስ ሁሴን፣ የዳሸን ባንክ ማርኬቲንግ እና ብራንዲንግ ዳይሬክተር አቶ እንዳለ ገብረስላሴ፣ የባንኩ የወላይታ ቀጠና ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ታዲዮስ ተስፋዬ እና የባንኩ የአርባምንጭ አካባቢ ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል አለማየሁ ተገኝተው ድጋፉን አበርክተዋል።
 

 

 

 

 

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram