Select Page

ዳሸን ባንክ በ4ኛው የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ማይንቴክስ ኢትዮጵያ) ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

ዳሸን ባንክ በማዕድን ሚኒስቴር አዘጋጅነት ለ4ተኛ ጊዜ በአዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ማይንቴክስ ኢትዮጵያ) ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት በተከፈተው ኤክስፖ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የማዕድን ሚኒስትሩ ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች ተገኝተዋል፡፡

የማዕድን አውጪዎች፣ አምራቾች፣አቅራቢዎች እንዲሁም ኤክስፖርተሮችና ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን እየተሳተፉበት  በሚገኘው በዚህ ኤክስፖ፣ ዳሸን ባንክ ለማዕድንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተዋንያን ያቀረባቸውን በርካታ አገልግሎቶች ከማስተዋወቅ ባሻገር ከዘርፉ አልሚዎችና ነጋዴዎች ጋር የስራ የትስስር ውይይቶችን አከናውኗል።

ከኅዳር 4 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው የማይንቴክስ ኢትዮጵያ ኤክስፖ ዳሸን ባንክ  ለዘርፉ አምራቾችና አቅራቢዎች ያቀረባቸውን አገልግሎቶች ከማስተዋወቅ ባሻገር፣ በዳሸን ሱፐር አፕ በቅርቡ የቀረበውን የዳሸን ዕድል ጨዋታ ጨምሮ ዘርፈ-ብዙ አገልግሎቶቹን ለጎብኚዎች እያቀረበ ይገኛል፡፡

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram