Select Page

ዳሸን ባንክ ቡታጅራ ከተማ ከሚገኙ ደንበኞቹ ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

ዳሸን ባንክ በቡታጀራ ከተማ ከሚገኙ የባንኩ ደንበኞች፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ሰሞኑን የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመርሃ-ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አመን ጀማል የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በከተማው በአካል በመገኘት ከደንበኞች ጋር ምክክር ማድረጋቸውን አድንቀው ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ከዳሸን ባንክ ጋር በትብብር ለመሠራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል ።

የዳሸን ባንክ የወላይታ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ተስፋአለም መንግስቴ በበኩላቸው መደረኩ የደንበኞችን ሃሳብ በአካል ተገኝቶ በማድምጥ እና ተገልጋዩ መሠረት ያደረጉ የባንክ አገልግሎቶች ለመስጠት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የዳሸን ባንክ አገልግሎቶችን ለማሻሻል ጥናት ላይ የተመሰረት ዘርፈ-ብዙ ስራዎች እየተተገበሩ መሆናቸውን ግልፀው፣ ደንበኞችም በቀጣይ ከባንኩ ጋር ተቀራርበው አብረው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram