Select Page

ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ 914 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር አቀረበ

ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ 914 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር አቀረበ

ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ደንበኞች 914 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 257.5 ሚሊየን ዶላር ለነዳጅ ግዥ የቀረበ ነበር፡፡

ባንኩ እ.ኤ.አ በሃምሌ ወር 2025 ብቻ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ 112.6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ማቅረብ ችሏል፡፡ ከዚህም ውስጥ 33.9 ሚሊየን ዶላር ለነዳጅ ግዥ የቀረበ ነው፡፡

ዳሸን ባንክ በዚሁ ወር 73.1 ሚሊየን ዶላር የተለያዩ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እንዲውል አቅርቧል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወደተለያዩ የውጭ አገራት ለሚጓዙ ደንበኞቹ 5.6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማቅረብ ችሏል፡፡

ዳሸን ባንክ በነሃሴ ወር የመጀመሪያ ስድስት ቀናት እንዲሁ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞች 11 ሚሊየን ዶላር አቅርቧል፡፡

ዳሸን ባንክ ደንበኞቹ የሚያቀርቧቸውን የውጭ ምንዛሬ ጥያቄዎች ለማርካት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram