Select Page

ዳሸን ባንክ ብቸኛ የባንክ አጋር  የሆነበት ሐዋሳ ግማሽ ማራቶን በሃዋሳ ከተማ ለ14ኛ ጊዜ በድምቅት ተካሄደ

ዳሸን ባንክ ብቸኛ የውድድሩ የባንክ  አጋር የሆነበት እና ለ14ኛ ግዜ በሃዋሳ ከተማ የተደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ  የ8 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተካሄደ ።

ውድድሩን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ዳሸን ባንክ  ባዘጋጀው  ልዩ መድረክ ላይ የባንኩ የተለያዩ አገልግሎቶቹን በተለይም ዳሸን ሱፐር አፕን ለተሳታፊዎች አስተዋውቋል ።

በውድድሩ መርሃ-ግብር ላይ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች  ለአሸናፊ ተወዳዳሪዎች በዳሸን ባንክ የሃዋሳ ቀጠና ጽ/ቤት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አስናቀ ደምሴ አማካኝነት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ብቸኛ የባንክ አጋር ሆኖ ለረዥም ጊዜ አጋር የሆነው ዳሸን ባንክ አዲስ አበባ የሚካሄደውን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ላይ በሚደረጉ ውድድሮች በመሳተፍ ከሚሰጠው የባንክ ዘርፍ አገልግሎት ባሻገር በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ እራሱን እንዲያደበርና ጤናው እንዲጠበቅ የበኩሉን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ይገኛል ።

በቀጣይም የ2018 ዓ.ም “ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” በጅማ፣በቆጂ፣በአርባምንጭ እና በሐረር ተመሳሳይ ውድድር ይካሄዳል።

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram