ዳሸን ባንክ ብቸኛ የባንክ አጋር የሆነበት የሳፋሪኮም “ቅድሚያ ለሴቶች” 5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በድምቀት ተካሄደ
ዳሸን ባንክ ብቸኛ አጋር የሆነበት የሳፋሪኮም “ቅድሚያ ለሴቶች” 5ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተካሂዷል ።
በውድድሩ መነሻ ቦታ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ታዋቂ አርቲስቶች እና ሌሎች በተለያዩ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ተምሳሌት ሴቶች ተሳታፊዎችን አበረታተዋል ።
በውድድሩ ላይ ከ35 ደቂቃ በታች ለጨረሱ ተወዳዳሪዎች የዳሸን ባንክ ቺፍ ፒፕል ኦፊሰር ወ/ሮ ሕይወቴ ከፈለኝ ሽልማት ያበረከቱ ሲሆን፣ በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ተሸላሚ ሴቶችን ደግሞ የዳሸን ባንክ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ አየለ ተሾመ ሸልመዋል።
መሐሃ-ግብሩን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ዳሸን ባንክ ባዘጋጀው ልዩ መድረክ የባንኩ የተለያዩ አገልግሎቶቹን በተለይም ዳሸን ሱፐር አፕን ለተሳታፊዎች አስተዋውቋል ።
ዳሸን ባንክ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ብቸኛ የባንክ አጋር ሆኖ ለረዥም ጊዜ የቆየ ሲሆን፣ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ላይ በሚያደርጋቸው ውድድሮች ላይ በአጋርነት በመሳትፍ ከሚሰጠው የባንክ ዘርፍ አገልግሎት ባሻገር በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ ራሱን እንዲያደበርና ጤናው እንዲጠብቅ የበኩሉን አስተዋጽዎ በማበርከት ላይ ይገኛል ።
