ዳሸን ባንክ ብቸኛ የባንክ አጋር የሆነበት የቡና ዐውደ-ርዕይ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ዳሸን ባንክ ብቸኛ የባንክ አጋር የሆነበት የቡና ዐውደ-ርዕይ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
የዐውደ-ርዕዩ ተሳታፊዎች ግብይት በሚፈጽሙት ወቅት የተቀላጠፈ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነም የዳሸን ባንክ አንድነት ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ብርሐኑ ተናግረዋል ።
ባንኩ በትላልቅ ሐገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሆነ የሚያነሱት አቶ ሳሙኤል የቡና ወጭ ንግድ ዘርፍ ደግሞ አንዱ እንደሆነ አመላክተዋል።
በዐውደ-ርዕዩ ላይ ቡና ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ተቋማት ባንኩ አጋር መሆኑን የሚያሳይበት መድረክ እንደሆነም አብራርተዋል ።
የዐውደ-ርዕዩ ተሳታፊ የሆነው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የአግሮ ክላስተር ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፈለቀ ታደሰ በበኩላቸው የቡና መገኛ ሐገር እንደመሆናችን ዘርፉን ለማነቃቃት መስራት ይገባናል ተብለዋል ።
ዐውደ- ርዕዩ ይህን ሐሳብ የሚደግፍ በመሆኑ የሚበረታታ ነው ያሉት አቶ ፈለቀ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በመስኩ ያለውን ጉልህ አበርክቶ እንደሚያስቀጥል አስረድተዋል።
በዐውደ-ርዕዩ ላይ ቡናን እሴት ጨምሮ መላክና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዩች ዙሪያ የፓናል ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ዳሸን ባንክን ወክለው የባንኩ ኮርፓሬት ባንኪንግ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ግርማ ተሳትፈዋል።
