Select Page

“ዳሸን ባንክ አርዓያ የሚሆን ተቋም ነው” ከዳሸን ባንክ ጋር የሚሰሩ ሐገር በቀል ግብረ ሠናይ ድርጅቶች

 

ዳሸን ባንክ ማሕበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት እያከናወነ ያለው ተግባር አርዓያ የሚያደርገው ነው ሲሉ የሐገር በቀል ግብረ ሠናይ ድርጅቶች ገለጹ፡፡

የአቢዘር ማሕበረሰብ አቀፍ የልማት ድርጅት የቦርድ ሠብሳቢ የሆኑ አቶ ተስፋየ ተመስገን ድርጅታቸው የዳሸን ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የረጅም ዓመት ደንበኛ መሆኑን ገልጸው፤ ባንኩ ስራችንን አጠናክረን እንድንቀጥል እያገዘን ነው ብለዋል፡፡

አቢዘር የማሕበረሰብ አቀፍ የልማት ድርጅት ከ7ሺህ በላይ አባላት ያሉትና ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትና ታዳጊዎችን (የቲሞችን) በተለያየ መልኩ እየደገፈ የሚገኝ ተቋም እንደሆነ አቶ ተስፋየ አብራርተዋል፡፡

አሁን ላይ ድርጅቱ ከ250 በላይ ለሆኑ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትና ታዳጊዎች የአልባሳት፣ምግብና ሌሎች ድጋፎችን እንዲያገኙ እንዲሁም ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ እገዛዎች ይደረጋል ብለዋል፡፡

ዳሸን ባንክ መሰል የማሕበረሰብ አቀፍ የልማት ስራዎች ይሳኩ ዘንድ አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኝ እንደመሆኑ ምስጋናችን ከልብ ነው ብለዋል የቦርድ ሠብሳቢው፡፡ ድርጅቱ አሁን ላይ በዳሸን ሱፐር አፕ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት ውስጥ መካተቱ ስራውን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳም ነግረውናል፡፡

በተያያዘ ስለ’ኔ የሴቶች አቅም ግንባታና የበጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አዚዛ ሙሣ በበኩላቸው ድርጅታቸው ሴቶችን ማብቃትና መደገፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ አንስተው ዳሸን ባንክ ስራቸውን በተሻለ ለማስፋት እያገዛቸው እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ባንኩ ማሕበራዊ ሃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ተቋሙን ምሣሌ የሚያደርገው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ድርጅቱ ከዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተው ተቋማቸው አሁን ላይ በዳሸን ሱፐር አፕ ውስጥ መካተቱ ሰዎች ባሉበት ሆነው ተቋሙን መደገፍ እንዲችሉና የበጎ አድራጎት ስራውን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ሌላኛው ግብረ ሠናይ ድርጅት በረካ ልማትና በጎ አድራጎት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጅብሪል ኢብራሒም በበኩላቸው ማህበራቸው ልማትና በጎ አድራጎት ስራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከዳሸን ባንክ ባንክ ጋር በአጋርነት እየሰሩ የሚገኙት እነኝህ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች በረመዳን፣ኢድ እና የዓረፋ በዓላትን በመሰሉ ወቅቶች አቅመ ደካሞች ደስ ብሏቸው እንዲያሳልፉ አባላቶቻቸውን በማስተባበር ድጋፍ እንዲደረግ እየሰሩ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

ዳሸን ባንክ መሰል ግብረ ሠናይ ስራዎች እንዲስፋፉና እንዲጠናከሩ እያደረገ የሚገኘው ተግባር ምስጋና የሚቸረው እንደሆነ የገለጹት የስራ ሐላፊዎቹ ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች  መልካ የኢድ-አልአድሐ አረፋ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram