ዳሸን ባንክ አጋር የሆነበት በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ ቢዝነስ ማህበር ዓመታዊ ፕሮግራም ተካሄደ

ዳሸን ባንክ አጋር የሆነበት በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ ቢዝነስ ማህበር ዓመታዊ ፕሮግራም ተካሄደ
ዳሽን ባንክ አጋር የሆነበት በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ የቢዝነስ ማህበር ዓመታዊ ፕሮግራም ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የኔዝርላንድ ኢምባሲ ቅጥር ግቢ “ብሪጂንግ ቦርደር” በሚል መሪ ሀሳብ ተካሂዷል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመነት ላይ የተሰማሩ የአውሮፓ ባለሀብቶች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር የትውውቅና በአጋርነት አብሮ በሚሰራባቸው ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ዕድል ፈጥሯል፡፡
በሁነቱ ላይ ከ250 በላይ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኔዘርላድ ባለሀብቶች፣ የአወሮፓ ህብረት የቢዝነስ ማህበር ተወካዮችና ዲፕሎማቶች ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ዓመታዊው የኔዝርላንድ ቢዝነስ ማህበር ፕሮግራም በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችን የሚያገናኝና በኢትዮጵያ የሚገኙ ዕምቅ የኢንቨስትመንት ዕድሎች የሚተዋወቁበት መድረክ ነው፡፡
በዝግጅቱ ላይ በአቶ አየለ ተሾመ የባንኩ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር የተመራ ቡድን ተሳትፎ ከተለያዩ የቢዝነስ ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።
