ዳሸን ባንክ አጋር የሆነበት የሴቶች 5 ኪ.ሜ ታላቁ ሩጫ ቅድመ-ውድድር በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ተካሄደ
የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ከመደረጉ አስቀድሞ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት በሚዘጋጀው የማነቃቂያ ቅድመ-ውድድር መርሃግብር ላይ ዳሸን ባንክ ተሳታፊ ሆነ፡፡
በማነቃቂያ መርሃ-ግብሩ ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ጨምሮ በተማሪዎች መካከል የዱላ ቅብብል የሩጫ ውድድር የተካሄደ ሲሆን፣ ዳሸን ባንክም ለአሸናፊ ሴት ተወዳዳሪዎች ያዘጋጀውን ልዩ ሽልማት አበርክቷል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ለእንስት ተማሪዎቹ ስለ ባንኩ 30 ዓመት የባንክ አገልግሎትና ዳሸን ባንክ ለኢንዱስትሪው በልዩነት ስላቀረበው የዳሸን ሱፐር አፕ ዘርፈ- ብዙ አገልግሎት ገለፃ ቀርቧል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ብቸኛ የባንክ አጋር ሆኖ ለረዥም ጊዜ የቆየው ዳሸን ባንክ መጋቢት 13 ለሚደረገው 23ኛው የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተሳታፊዎች ከየካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በዳሸን ሱፐር አፕ የ10% ቅናሽ በማድረግ ምዝገባ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር የሆኑት ሕሊና ንጉሴ በእቴጌ መነን አዳሪ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት የተዘጋጀው መርሃ-ግብር በየዓመቱ የሚካሄድና የቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር አንድ አካል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ ለረዥም ጊዜ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ሲሰሩ ከቆዩ ተቋማት አንዱ ዳሸን ባንክ መሆኑን ያስረዱት ሕሊና፣ ዳሸን ባንክ በተለይ ሴቶች ላይ አተኩሮ እንደሚሰራና ይህም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚጋራው ትልቅ ዓላማ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
16,000 ሴቶች የሚሳተፉበትና በጉጉት የሚጠበቀው 23ኛው የ2018 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር እሑድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ ይከናወናል፡፡
