ዳሸን ባንክ አጋር የሆነበት የቡና አውደ-ርዕይ ተከፈተ
ዳሸን ባንክ አጋር የሆነበት የቡና አውደ-ርዕይ (Coffee Feast) በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተከፍቷል።
በአውደ-ርዕዩ ላይ ቡና ላይ የተሰማሩ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል።
ዳሸን ባንክ በአውደ-ርዕዩ ላይ የተሟላ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፤ ተሳታፊዎች ዳሸን ሱፐር አፕ መተግበሪያን በመጠቀም በቀላሉ ግብይታቸውን እየፈጸሙ ይገኛሉ።
የአውደ-ርዕዩ ተሳታፊዎች ዳሸን ባንክ በአጋርነት እየሰራ መሆኑ ግብይታቸውን በቀላሉ ለማቀላጠፍ እንዳገዛቸው ገልጸዋል።
ዛሬ ኅዳር 13/2018 ዓ.ም በይፋ በተከፈተው አውደ-ርዕይ ላይ በቡና ዘርፍ ላይ የሚታዩ አበረታች ውጤቶችና እያጋጠሙ የሚገኙ ተግዳሮቶችን በተመለከተ የፓናል ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
አውደ ርዕዩ እስከ ነገ እሑድ ኅዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይቀጥላል።
