Select Page

ዳሸን ባንክ ከሐንስ ኬር ጋር በመተባበር ዳግም ጥቅም ላይ የሚውል የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ

“ሴቶችን ማገዝ ሃገርን ማገዝ እንደመሆኑ ዳሸን ባንክ ከአጋር ተቋማት ጋር በመሆን የሚያደርገውን ድጋፍ ያስቀጥላል” -የደሴወርቅ  ጥላሁን ዳሸን ባንክ ከሐንስ ኬር ጋር በመተባበር  ዳግም ጥቅም ላይ የሚውል የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ

ባንኩ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር 500 የንጽሕና መጠበቂያ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስረክቧል።     ድጋፉ ለኮሌጁ ተማሪዎችና ድጋፍ ለሚሹ ሌሎች ሴት ተማሪዎች ተበርክቷል።

በድጋፍ  ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሪቴል ባንኪንግ መምሪያ ኃላፊ የደሴወርቅ  ጥላሁን”ሴቶችን ማገዝ ሃገርን ማገዝ እንደመሆኑ ዳሸን ባንክ ከአጋር ተቋማት ጋር በመሆን  የሚያደርገውን ድጋፍ ያስቀጥላል” ብለዋል።

የሐንስ ዊዝ  ኬር  የንጽህና መጠበቂያ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ሐናን አህመድ ሴት ልጅ የማሕበረሰቡ ወሳኝ አካል ነች ብለን ስለምናምን ከባንኩ ጋር አብረን እንሰራለን ሲሉ አስረድተዋል።

በሴቶች ዙሪያ ብዙ ስራዎች ይጠበቅብናል ያሉት ስራ አስኪያጇ ከዳሸን ባንክ ጋር በመሆን በቀጣይም ተመሳሳይ ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባራትን እናከውናለን ብለዋል።

የሐረሪ ክልል የሴቶችና ሕጻናት ጉዳይ  ቢሮ  ም/ኃላፊ መፍቱሃ ዓሊ  በበኩላቸው በንጽህና መጠበቂያ እጥረት ምክንያት በርካታ ሴት ተማሪዎች ከትምህርት እንደሚቀሩ ጠቁመዋል።

ም/ኃላፊዋ ዳሸን ባንክ ላደረገው ድጋፍ “እናመሰግናለን” ብለዋል።

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram