ዳሸን ባንክ ከማክስ ብሪጅ የትምህርትና ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ነው
ዳሸን ባንክ ከማክስ ብሪጅ የትምህርትና ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ነው
ባንኩ ድጋፍ ያደረገበት የስልጠናና የልምድ ልውውጥ መርሐ-ግብር በፋይናንስ አገልግሎቶች የሸሪዓህ አስተዳደር ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎል።
በመርሐግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የማክስ ብሪጅ የትምህርትና ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብዱ ሰኢድ ዳሸን ባንክን የመሰሉ ተቋማት የስልጠናና ልምድ ልውውጥ መድረኩ እንዲሳካ በማድረጋቸው እንደሚመሰገኑ ተናግረዋል።
ስልጠናው የረጅም ዓመት ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚሰጥ እንደመሆኑ ተሳታፊዎች ተጨማሪ ግንዛቤ እንዲያገኙ እንደሚያግዛቸው አመላክተዋል።
ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት ፕሮፈሰር አብደልአዚም አቡዘይድ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎትና የሸሪዓህ አስተዳደርን በተመለከተ ልምዳቸውን እያካፈሉ ይገኛሉ። ለስልጠናው ተሳታፊዎች በምሳሌ የተደገፉ ማብራሪያዎችን የሰጡ ሲሆን ለተሳታፊዎች የጥያቄና መልስ መድረክ ተዘጋጅቷል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው በዘርፉ የረጅም ዓመት ልምድና አቅም ባላቸው ባለሙያዎች እየተሰጠ በመሆኑ ተጠቃሚ መሆናቸውን አመላክተዋል።
የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ በዕውቀት እንዲመራና ዘርፉ እንዲበረታታ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
ሸን ባንክ የኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር ቋሚ አባል በመሆን ተመሳሳይ ገንቢ ስራዎችን እየተገበረ ይገኛል።
ዳሸን ባንክ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ ዘርፍ እንዲያድግ የበኩሉን አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል።
ባንኩ በዓለም አቀፍ ደረጃም The Accounting and Auditing Organization for Islamic Financial Institutions (AAOIFI) ቋሚ አባል ነው።