Select Page

ዳሸን ባንክ ከሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሠራተኞች ስልጠና ሰጠ

ዳሸን ባንክ ከሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ያተኮረ ስልጠና በዛሬው እለት በግዮን ሆቴል ሰጥቷል፡፡

በዳሸን ባንክ የኢቲክስና ኮንዳክት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ጥላየ እንየው ስልጠናው ሠራተኞች በጉዳዩ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረቸው በማለም የተዘጋጀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ባንክ የሚገነባው በካፒታል ብቻ ሣይሆን በደንበኞች እምነት፣በሠራተኞች ታማኝነትና በባንኩ የሥነ-ምግበራዊ ባህል እንደሆነም በስልጠናው መክፈቻ ላይ አመላክተዋል፡፡

የሥራ ኃላፊዎች በየጊዜው የሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች በባንኩ አፈጻጸም፣በደንበኞች እርካታ፣በሠራተኞች  ሥነ-ምግባርና በባንኩ ስም ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ እንደመሆናቸው ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት ተከታታይ ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

ስልጠናው 140 ለሚደርሱ የባንኩ ኤሪያ ማኔጀርስ፣ኦፕሬሽን ማኔጀርስ እና ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ተሰጥቷል፡፡

    

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram